Injera le-tenaye

Injera le-tenaye Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Injera le-tenaye, Fast food restaurant, Reigate.

መፈፅም ዘዐቢይ፥ቀብር ዘጥልምያኮስ፤ ቅማሏን እና ትኋኗን አግኙ። (ዐቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ)Posted by admin | November 22, 2020 | 0መፈፅም ዘዐቢይ፥ቀብር ዘጥል...
10/11/2025

መፈፅም ዘዐቢይ፥ቀብር ዘጥልምያኮስ፤ ቅማሏን እና ትኋኗን አግኙ። (ዐቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ)
Posted by admin | November 22, 2020 | 0
መፈፅም ዘዐቢይ፥ቀብር ዘጥልምያኮስ፤
ቅማሏን እና ትኋኗን አግኙ።
ዐቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ
ለመግቢያነት፦የሐዲስ፡ዓለማየኹ።
(ባ፲፱፻፳፰፡ዓ.፡ም.፥ዐርበኝነት፡ሲወጡ፥ለሕዝብ፡ከበተኑት፡ቀስቃሽ፡ግጥም፡ውስጥ፡የተቀዳ።) አያያዝኩ፦

እናት፡ኢትዮጵያ፡
ውዲቱ፥ውዲቱ፥
በሦስቱ፡ቀለማት፡
የተሸለምሺቱ፥
ነጻነት፡የሚሽር፡
ቢመጣብሽ፡ብርቱ፥
ደማችን፡ይፈሳል፥
አይቀርም፡በከንቱ።
ላንቺ፡የማይረዳ፡
ሳለ፡በሕይወቱ፥
በረከትሽን፡ይንሣው፡
እስከ፡ዕለተ፡ሞቱ።
አመሰግናለሁ ክቡር ዶክተር ሎሬት የሐዲስ፡ዓለማየኹን።
003.JPG
የታሪክ ትንቅንቁ በትግሬ ክፍለ ሃገር ተጧጥፏል፤መንግሥት(በሥመ ብልፅግና) እና “ምን አገባህ?” የሚል የሕውሃት(ዘረኝነትን የሚደግፍ)ቡድን ናቸው የሚገዳደሉት።”መፈፅም ዘዐቢይ፥ቀብር ዘጥልምያኮስ”የተባለውም ለእነዚሁ ሁለቱ ወገኖች የቀረበ ነው።በአንድ ወገን ይህን የትግሬ”ክፍለሓገር ሕዝብ” በዕምቢተኛነት አመፅ አግቶ፤በሕገመንግሥት ጭምብል በራሳቸው ሥልጣን በፈጠሩት ቡድን የሚመራ፣በትዕቢት እየተቆዘረ ለሌላው ደንታ በሌላቸው፣ሰዎችን በሚመስሉ እና የሰው ቆዳ በለበሱ ርኩሶች የሚዘወር ሰበበኛ ገዳይ አሸባሪ ፓርቲ ነው።
በሌላው በኩል በመንግሥት ሥልጣን ሳይወዱ-በግድ ትዕግሥት ለገዳዩ ያምበሸበሹት ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አህመድ፣ በአንፃራዊነት የመቶ ሚሊዮን ሕዝብ ተወካይነታቸውን ባለመዘንጋት፣ለስድስት ሚሊዮኑ ሰዎች በደም ሳይፈርሙ፦ተንቀልቅሎ ገዳዩ ጦርነቱን በማስጀመሩ በትዕስት መሪ አማካኝነትም ፊሽካ እንዲነፉ ያስደረጉ የፖለቲካ ቀዶ-ጠጋኝ ዶክተር የተደረገ ፍልሚያ ነበር፤እነሆ ዓለም በአደባባይ እያየው እና ገዳዮቹን እየረገማቸው ለሕዝብ ክህደታቸውን ሲያጋልጥ፦ለሁለቱም በየግብራቸው”መፈፅም ዘዐቢይ ተብሎ”ለዶክተር ዐቢይ እንደተሰጠው፣የሕውሃት ቡድን ጉዳይ ደግሞ፣”ቀብር ዘጥልምያኮስ”በሚል ትግሉ እየተጠናቀቀ ይገኛል።
መቼም የኢትዮጵያን ነፃነት እና አንድነት ለማስጠበቅ ያለፉት ትውልዶቻችን የበለጠውን መስዋዕትነት ባይከፍሉ ኖሮ ኢትዮጵያችን በነፃነት ተጠብቃ እስከዛሬም አትኖርም ነበር።በተፃራሪው ደግሞ አንድነቷ እንዳይኖር በባዕዳን በጥቅማ-ጥቅም ተገዝተውም ሆነ ተታለው ሕዝቦቿን እያለያዩ ሊበታትኑን ሌትተቀን በመሰሪ ተንኮሎች የጠላት መሳለቂያ እያጋደሉን ያደረጉን ውርደታሞች በታሪክ ተመዝግበዋል።ይሁንና የእናት ሆድ ዥንጉርጉር ነውና፣ጡቷን መንከስ ብቻ አይደለም ራሷን ኢትዮጵያን ለመሸጥ ያልፈነቀሉት ድንጋይ፣ያልመዘዙባት ሠይፍ አልነበረምና፤ቢያንስ ለሃምሳ ዓመታት አገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው በራሳችን ዜጎች ሰበብና ምክንያትን እያስታከኩ በደም ያጨማለቁን የሰዎች ሥም ዝርዝር ታሪክ አላት።
የጀግኖችም ሆነ የከሃዲዎች በነፍስወከፍ የተፃፉም ቢሆን በንፁህ ሕሊናቸው ፀንተው ከተሰዉት ሐይማኖታዊ አባት አቡነ ጵጥሮስን በግምባር ቀደምትነት እናስታውሳቸዋለን፤በዘመናችን ደግሞ ከእነ ንፁህ ሕሊናቸው ይህቺን ዓለም የተሰናበቱ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ነብሳቸውን እግዚአብሔር በመንግሥተ-ሰማያት ያሳርፋትና ፍፁም ዝም ሳይሉ፣ጠመንጃ ሳያነሱ፤በእሳት ልሳናቸውና በመራር ቃላታቸው እየለበለቡ ዕድሜ ልካቸውን መንግሥታትን እንደተዋጉ ሁላችንም እናውቃቸዋለን።በእርሳቸውም የትግልት ስልት ምክንያት በዘመነ-ቴክኖሎጂ ሐቁን በሕዝብ መገናኛ ሚሳይል እያስወነጨፉ የሚደበድቡ ጠንካራ ዜጎች ተፈጥረውም ሰምተናል።የሚያሳዝነው ደግሞ”ሰውን በመግደል የፈለግነውን ማስፈፀም እንችላለን”ብለው የሚያምኑና የሚተገብሩ፤ራሳቸው እንዳይሞቱ ግን፣ከለቅሶ ጀምሮ የማያደርጉት ነገር እንደሌለ ማየታችን ነው።
የእኛው ትውልድ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ናቸው የምንላቸው ለእነዚያ የፋሺሽት-ሕውሃት ሰው በላዎች ዛሬም በድብቅ ጠበቃዎች ሆነው ያስረግጡናል።”ከትግሬዎቹ መካከል-“ሕውሃት ነን” የሚሉት በሁለተኛ የዓለም ጦርነት ወቅት”ናዚዎች”በመሆናቸው ሲኩራሩ እንደነበሩት ገዳዮች ነገ በሕዝብ የሚሳደዱቱ ናቸው።፣በዚህ ብቻም አላበቁም “እኛ ከሞትን ሰርዶ አይብቀል”ብለው ሊያጠፉን ሲውተረተሩ፣ወገባቸውን በሕዝብ አመፅ ተቀጥቅጠው ሽባ እንደሆኑ አንገታቸው ተቆርጦ፣እየወደቁ እየተንፏቀቁ መቀሌ በእንቅጥቅጥ ከሸመቁ ድፍን ሁለት ዓመታት ካለፋቸው ሰነባበተ። “ያ!”የመከራ ወቅት ግን በይቅርታ እና በፍቅር ሥም ሠላምን በአገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ለመፍጠር በሚል “በአደባባይ” ስምምነታቸው ቢነገርም የኢትዮጵያ ግምባር ቀደሙ ጠላት “ዘረኝነትን የዘራው፣ሕውሃት”ያለ እኛ ኢትዮጵያ የለችም” ብለው ዛሬም ይገድሉናል፣በትክክል እየገደሉን እና እያጋደሉን ይገኛሉ፤ለኢትዮጵያ ችግር ሰበቦቹም ሆኑ ምክንያቶቹ አሁንም ርዝራዦቹን የደበቀው “ሕውሃት”የተባለ የሽብርተኛ ቡድን ብቻ ነው፣ሌላው አገላለፅ ከዝባዝንኬ ይቆጠራል።
ስለዚህም ዶክተር አቢይ አህመድ ማሰሪያ የትግላችንን ልጥ ካለበት ፈልጎና መርጦ ካመጣ በኋላ በሚገባው የዓለም አቀፍ ሕግ ተጠፍሮ እንዲታሰርና በታሪክ ማሕደር ውስጥ እንደነዚያ ፋሺሽቶ ናዚዎች ማስደረግ ይጠበቅበታልና”መፈፅም*ዘዐቢይ መሆኑንና የከሃዲዎች መጨረሻ ደግሞ ቀብር ዘጥልምያኮስ በአንፃሩ መፈፀሙን ማረጋገጥ ይኖርበታል።
ስለዚህም ነው ቅማሏን እና ትኋኗን አግኙ፤ያለበለዚያ ለሠይጣን ደንግጦ ሬሳ መቁጠሩ መፍትሄ እንደማያመጣ ደጋግሜ የገለፅኩት።ወገን እንግባባ ዛሬም አትሞኙ፤ችግሩን ለማጥፋት ቅማሏን አግኙ።ትሗኗ ላይ አሁን ካልወሰድን እርምጃ፤ተስቦው አይቀርም ለመዳን ግን እንጃ::ለዚህ ነው እንደገናም በየጥጋጥጉ፤ጊዜ ያብከንነው የሌለ አትፈልጉ::
እባካችሁ ወገኔ ዛሬም አትሞኙ፤ቅድሚያ ይቺን ፋሺሽት ትኋኗን አግኙ።ጥርሷን ከተከለች ቅማል እንኳን ባቅሟ ፤ጥብጣብ ታስፈታለች አሳብጧት ደሟ።ሺህ ቦታ መቶ ጥግ በየጉራንጉሩ፤ማከክ መሞዠቁ አካል መቆፈሩ፤ለሰይጣን ደንግጦ ሬሳ መቁጠሩ፤ መፍትሔ ባይሆንም እንደው ለጅምሩ፤ገዳይ እንዳይቀድመን:-ከልብ ግን አምርሩ።ለሕዝብ በመቆማችሁ ባንዳ የጠላችሁ፤ የኢትዮጵያ ሕላዌ ያንገበገባችሁ።ለአገር የምትጓጉ፤ትርጁማን ፈልጉ!!!እናም ለነፃነት እንዲቆም በዝና፤ዛሬውኑ አምጡለት የመቅደምን ዜና።ለነፃነት ፃፉ በሙያችሁ ሁሉ፤ለፍትህ ለፍፉ ያሻችሁን በሉ።ሁሉም ሆኖ ግና ቃል ግቡልንና፤ አምጡልን በዝና የደም-ዋጋ ዜና!!!…….መንግሥት ተጠልለው ለጥቅም የማሉ፤የሕዝብን ያቀለሉ ጋዜጠኞች አሉ።ሕዝብን የሚወጉ፤ከሕዝብ የመሸጉ።ፋሺሽቱ-ወያኔ በኦሮሞ ሥም ታገል፤እኛን እንዳጋደልክ ሩጥ ወደገደል።ዛሬም ዋሻ ሆነውበሕዝብ እያላገጡ፤በድብቅ ትዕዛዝ አሉ የሚሰጡ።ከሸበጥ ተነስተው አየር ላይ የወጡ፤በወንጀል በዝርፊያ አብጠው የቀበጡ፤በግፍ በጭካኔ ሕዝብን የረገጡ፤ዛር ሳይሞትባቸው ሳይገለበጡ፤ከላይ ተከስክሰውምድር ላይ ሳይፈርጡ፤ እንደወንጀላቸው በሞት ሳይቀጡ፤እናት ሆድ አይገቧት የትም አያመልጡ፤አይማሩም ፍፁም እንዲህ እንዳላገጡ። ቀረ’ኮ ይሉኝታ ቀረ’ኮ መ-ደበቅ፤በጉጅሌ ጉያ ሕዝብ ላይ መሳለቅ።በይሉኝታ ዝምታ ምንም የማይባል፤አይነደረቅ ሌባ:-ቃጭል ይዞ ይገባል።ዘንዶው ቢቀረንምጇሗር እባቡም ተይዟል፤የኢትዮጵያ ትግል!!!በጨካኞች ጦዟል።በሰላም መታገልብለን ይሻለናል፤ እናውቃለን ያሉት፣ዛሬም ያጋድሉናል።ዘንዶውም አይቀርምከያለበት አገር፤በእንፉቅቅ ይመጣል፣ከዋሻቸው ሳይቀር። እየተለቀመ አደራ እባቡንፍፁም እንዳትገድሉት፤ከሙሴ ተማሩ እንዲደርቅ ስቀሉት።እናም ተቀጥቅጦደሙ እየፈሰሰ፤ይነቃል በቅፅበትአፈሩን ከላሰ።አንገቱም ቢቁረጥ እየሞቶ ይኖራል፤በጥርሱ ሰው ገድሎመሞት ይጀምራል።ግና እስከዚያው ድረስጇሗር ያው እባብ ነው፤ሞቷል ብለን ሲገድል አይተን የማናምነው።ወገን እንግባባ ዛሬም አትሞኙ፤ችግሩን ለማጥፋት ቅማሏን(ትኋኗን)አግኙ።

አራራት ተራራ...*ኢትዮጵያ ማለት የቃሉ ትርጉም የተቃጠለ ፊት ማለት ሳይሆን ኢትዮጵያ ማለት “ለአምላክ የሚሰጥ የወርቅ ሥጦታ” ማለት ነው።ሲተነተንም ኢት=አምላክ፣ ፈጣሪ፣ እግዚአብሔር ማለት...
27/09/2025

አራራት ተራራ...
*ኢትዮጵያ ማለት የቃሉ ትርጉም የተቃጠለ ፊት ማለት ሳይሆን ኢትዮጵያ ማለት “ለአምላክ የሚሰጥ የወርቅ ሥጦታ” ማለት ነው።ሲተነተንም ኢት=አምላክ፣ ፈጣሪ፣ እግዚአብሔር ማለት ሲሆን ዮጵ= ቢጫ ወርቅ፣ ውድ ወርቅ፣ ልዩ ወርቅ ማለት ነው።
*ሊቀ ነብያት ሙሴን የአመራርነት ጥበብ ያስተማረው ኢትዮጵያዊው ዮቶር ነው። ስለዚህ ለእስራኤል ከፈርዖን ነጻ መውጣት የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሚና አለበት ማለት ነው።
*አሁንም የሊቀ ነብያት ሙሴ ሚስት ሲጳራ ኢትዮጵያዊት ነች።ሐበሻዊት ሲጳራ የኢትዮጵያዊው የዮቶር ልጅ ነች።አልአዛር እና ጌርሣም የሚባሉ ልጆችንም ወልደዋል። ሙሴ ይቺን ሴት በማግባቱ ወንድሙ አሮንና እህቱ ማርያም ያጉረመርሙበት ነበር።
* የመጀመሪያው ካህን መልከጼዴቅ ኢትዮጵያዊ ነው ይህ ካህን በክርስትና አስተምህሮ የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ተደርጎ ይቆጠራል።
*ከባቢሎን ዘመን አስቀድሞ የነበረው ብቸኛው የሰው ልጅ ቋንቋ (ግዕዝ) የሚገኘው ኢትዮጵያ/ቤተ ክርስትያን/ ውስጥ ነው።
* ጻዲቁ አባታችን የሄኖክ የልጅ ልጅ ኖኅ የተቀበረው ኢትዮጵያ/ጎንደር/ ውስጥ ነው።
* ኖኅ ራሱንና ልጆቹን ከንፍር ውኃ ያዳነባት መርከቡን ያሳረፋት ኢትዮጵያ ጣና አካባቢ ከሚገኘው አራራት ተራራ ላይ ነው።
*የመጀመሪያው ሰው አዳም የተፈጠረው ከአራት ባህሪያተ ስጋ ነው። ከእነዚህም መካከል ደግሞ የተፈጠረበት እሳት ውኃና ነፋስ የተገኘው ከኢትዮጵያ ነው። ከዚህም በመነሳት አዳምና ሄዋን ኢትዮጵያዊያን ናቸው። ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ ነች።
*ኖኅ በጣና ነበረ።ኖኅ የዘመኑ ፍጻሜ እሰሰከሚቀርብ ይኖር የነበረው በአራራት ተራራ ነው።የኖኅ መርከብ ሐመር ያረፈችበት ስሙ ሉባር ተራራ ይባላል።
(ገድለ አዳም፣157-167፣ኩፋሌ 8፥1)
*አራራት ተራራ 150 ሜትር ርዝመት አንባ ሊኖረው ግድ ይላል ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሐመር አሠራር የሚነግረን ይህንን ነው።
*ሌላው አራራት ተራራ ተያያዥነት ያለው ተራራማ ነው።መርከቧ ያረፈችበትና ኖኅ ወይን የተከለበት ተራራ ነው።ኖኅ አካባቢውን ሳይለቅ ከጥፋት ውኃው በኋላ 350 ዓመት ኖረ።የትም አልሄድም ኖኅ ካምን ይዞ ወደ አፍሪካ ምድር ሄደ የሚለው ልቦለድ ድርስት ነው።
*ሌላው የኖኅ መቃብር ከአራራት ተራራ አይርቅም።እርሱም በአሁኗ ጎንደር ከተማ ሲሞት በመቃብሩ ላይ ምንጭ ፈልቆ በርካታ ሰዎችን ይፈውስ ነበር።ሆኖም ፈጣሪ ለኖኅ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ በቤተመንግሥት አሳቦ የኖኅ መቃብር ሐውልት እንዲታነጽ ፈቀደ።(ያሬድ ግርማ,የጎንደር ታሪክ 1999 ዓ.ም.)
*የኖኅ ሚስት እሜቴ አይከል የተቀበረችው ጭልጋ ላይ ነው።በዚህም የጭልጋ ዋና ከተማ በስሟ አይከል ተባለች።ጭልጋ የአራራት ተራራ አዋሳኝ መሆኑ ይታወቃል።
*ሉባር የሚባል ከተራሮች መሃል የሚገኘው ጣና እንጅ ከአርመኒያው ቦታ የለም።የነጮች የፈጠራ ውሸት ነው።ያልተፈጠረን ታሪክ ሲነግሩን የቆዩት የአራራትን ተራራ ታሪክ ለመሻማት መሆኑ ግልጽ ይሁን።
*መጽሐፈ ኩፋሌ 9 ላይ እንደተብራራው ኖኅ ለልጆቹ ርስት ሲያከፋፍል ለሴም ጣናንና አባይን ተንተርሶ እስከ ግብፅ ዕጣ እንደወጣለት ይታወቃል።ግብፅ ለመነሻው ቦታ ሰሜን ናት።ግብፅ ለእስያ ምድር ሰሜን አትሆንም።
*አራራት ተራራ ለማየት በባህርዳር ከተማ ፊትለፊት 3 ዝቅተኛ ተራራዎች በጣና ሐይቅ ዳርቻ ማየት ይቻላል።ወይንም በዘጌ በኩል ሦስቱ ተራሮች ከስር በኩል አንድ ሆነው ከላይ በኩል ተለያይተው ይታያሉ።መርከቧ ያረፈችበት ቦታ ደልዳላ ሲሆን የመርከቧን ስፋትም መገመት ይቻላል።
*ወይንም አራራት ተራራ የይጋንዳ ተክለሃይማኖት ቤተ ከርስቲያን ያለበት ነው።መርከቧ ያረፈችው ከቤተ ክርስቲያኑ ጥግ ነው።መርከቧ ያረፈችበት ሉባር ተራራና ሌሎችም ቦታዎች እስከ አሁን ድረስ በአትክልት የታጀቡ ናቸው።የዘጌ ኗሪዎችም አትክልት በማትከል ብቻ የሚተዳደሩ ናቸው።
ዋቢዎች
1.የጎንደር ታሪክ ያሬድ ግርማ ሃይሌ 1999 ዓ.ም.
2.የ5000 ዘመነ ታሪክ ከኖኅ እስከ ኢህአዴግ መጵሐፍ 1 ፍስሐ ያዜ 2010 ዓ.ም.
3.መጽሐፍ ቅዱስ 81 መጽሐፍ 1980 ዓ.ም.በኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር
4.ገድለ አዳም ማሕበረ ቅዱሳን 2008 ዓ.ም.
5.አኤል ታማክ በጥጋቡ ተፈሪ 2011 ዓ.ም.
*በቴሌግራም ያግኙን.https://t.me/ethioi
*በቅርቡ በ YouTube ቻናል ስለምንመጣ ፕሮግራም እንዳያልፋችሁ subscribe በማድረግ ቤተሰብ ሁኑ።
https://www.youtube.com/channel/UC6m-V3zA2xrlwPPWtXLJ33A

“እናንተ እስራኤላውያን፣ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያውያን አይደላችሁምን?” …                   አሞጽ 9:7
28/08/2025

“እናንተ እስራኤላውያን፣ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያውያን አይደላችሁምን?” …

አሞጽ 9:7

25/08/2025
ADDIS ABEBA
10/07/2025

ADDIS ABEBA

የጀግና እንጉርጉሮከኦርዮን ወ-ዳዊት############“አንተም አበዛኸው ፡እኔንም መረረኝ”ቅማል አስተሳሰብህአካሌን ወረረኝ።አይረባ ዘጭ ዘጭ ፡እየገባህ ታረቅ፣ገሳ ዝናብ እንጅ ፡አያድንም መብ...
17/04/2025

የጀግና እንጉርጉሮ
ከኦርዮን ወ-ዳዊት
############
“አንተም አበዛኸው ፡
እኔንም መረረኝ”
ቅማል አስተሳሰብህ
አካሌን ወረረኝ።
አይረባ ዘጭ ዘጭ ፡
እየገባህ ታረቅ፣
ገሳ ዝናብ እንጅ ፡
አያድንም መብረቅ፣
ምከሩት ያንን ሰው ፡
ያን አጉል ደንቆሮ፣
እሳት ሊበላው ነው ፡
በገዛ እጁ ጭሮ፡፡
ትናንት ባደባባይ
ወጥተው ሲፎክሩ
እንደመሶሎኒ
ጭዳ ሆነው ቀሩ።
እነዚህም በፋኖ
ጭምብል ተከልለው፤
ይንፈራገጣሉ፥
አማራ ሳይቀድም
ኢትዮጵያ የለም ብለው።
ምክር አንሰማም ካሉ
ተዉዋቸው ይፍነኑ፤
ይንቁ ከእንቅልፋቸው
ትግሉ የምር መሆኑ።
የፈነነም ይፍነን፤
እኛም ዝግጁ ነን።
ለዘረኞች ሳይሆን
ለንፁሃን ደም ነው፤
ኢትዮጵያዊ ሲሞት
ዛሬም የምናዘነው።
ባንዳዎች ለዓመታት
የዘሩት ይህ ክፋት፤
ነበረ ዕቅዱ፤
ኢትዮጵያን ለማጥፋት።
ግና ሳይሆን ቀረ
ጠላትም አፈረ።
ደግሞ የመረረ ዕለት
አላርፍም ካለ ጣት፤
ሽንፈት ተቀብሎ
በግዱ ይዋጣት።
ግና ይሚያሳዝነው፤
ሲቀለድበት ነው።

ፋኖን ቀለዱበት።
#########xx
የእምቢዬአችን
መታወቂያ፤
ያመጻችን ስውር መውቂያ።
ግፈኛን ያራወጥንበት፤
ጠላትን የገረፍንበት።
ስንት ጀግና የሞተለት፤
በአገር ፍቅር የደማለት።
በነዚያ ክብር ባርበኞቹ፤
ቀለዱበት ሽፍታዎቹ።
ገዱ
"ጋዱ" ሆኖ፤
በእንቅዥቅዥ
ተፋጥኖ።
የእባብ
ተልመጥምጦ፤
በመነጽሩ
አጉረጥርጦ።
እየተጀነነ፤
እየተፎነነ፣
እየተቆነነ፤
እየተቧደነ፤
"ጋዱ" ጌዶር ሆነ፦ ፦ ፦። ።
በድህነት ዘመናችን፤
መበልፀግ ነው አሉ ጠላታችን።
እንደ ዘመነ መሳፍንት፥
በየጎጡ እየተሳለቁ ትናንት፤
ዘለሌን በትንቢት፥
ፈርሳሙን በጮማው፤
በገንዘብ በፍትፍት
ስልጣንም ለጠማው፤
እያከፋፈሉ
ሐቅ ታጋይ ተባሉ።
አገር በታጋዮች
እንክኳንስ ሊመራ፤
ተራው ሽፍታ ደግሞ
በፋኖ ሊጠራ፤
መጥፋት ነው ያለበት
በሚያጠፋው በደል፤
ቀድሞ ሕዝብ ሳይረሽን፥
ራሱ ይገደል።
አሳዛኝ ነው በጣም
ዐይነ ደረቅ ሌባ፤
ያለማፈር ቃጭል ይዞ
እንደሚገባ፤
በመግለጫ በአዋጅ
መቼ ነው የመጣው፤
እንክኳንስ ግምባሩ
ይሰማል ወይ ቁጣው።
ፋኖ ነን የሚሉን
በአማራ አንደበት፤
ግብሩን እያዋረዱ
በሥም ቀለዱበት።
እኒህ የሰው እበት፤
ፋኖን ቀለዱበት። See less

01/03/2025

ጥቁሩ ወርቃማ የኢትዮጵያ ድል

ኢትዮጵያዊው ዶክተር ዐቢይ ዘበሻሻ እኔም እልሃለው፥

ክበር በስንዴ
ክበር በጤፍ፤
ምቀኛህ ይርገፍ።

መቼም የኢትዮጵያ ታሪክ በሓቅ ትንታኔ ሲነሳ፤የውጭ ባዕዳን አህጉራት በጉድፍ መጠቅጠቃቸው በተጨባጭ መረጃዎች ይታወቃል።
ለምሳሌ በምርምር የብላርዚያ በሽታን እና መድሐኒቱን ያገኙት ኢትዮጵያዊው ዶር አክሊሉ ለማ ሲሆኑ፤የሮም መንግስትን በጦርነት ውጊያ ያሸነፉት በኢትዮጵያዊው ዳግማዊ አጼ ምንሊክ መሪነት አንደሆነ እንዳይታወቅ ብዙ ጥቃቅን ማደናበሪያዎችን ያጣብቃሉ፤ ዕውነቱ ጥቁሩ ኢትዮጵያዊ መሪ ንጉሠ ነገሥት ነበሩ።
የሚገርመው ውጊያው የተካሄደው በጣሊያን ሮማውያን አና በኢትዮጵያ መካከል አንደሆነ አየታወቀ የድሉን ውጤት እና የውጊያውን ቦታ በተለይ እንግሊዞች፣በታሪክ አመዘጋገብ ላይ የኢትዮጵያዊነቱን ሐቅ ዘ ባትል ኦፍ አድዋ ብለው ሰይመውታል ሲያድበሰብሱት ፤ በሐቁ ስንነጋገር የጦርነቱ ባለቤት በማን ሥም ይታያል፣በኢትዮጵያውያን ወይስ በአንድ አውራጃ ሥም፤የማን ጦርነት አና ድል አንደሆነ እንዳይታወቅ፤በክልል ወስነው የኢትዮጵያ መባሉን እንዲቀር ይመሰጥሩታል፤እናም በአድዋ እንዲደረግ የተወሰነው ጦርነት እናየ አድዋ ድል የሚባለው አራቱ ንዑሳን ድሎች ባለመነገራቸውና፣የኢትዮጵያ ድል መባል ያለበት የጦርነቱን ዕውነተኛ አራት የውጊያ ገጽታዎች እንዳልነበሩ አድርጎ በመሠሪነት በመነገራቸው ነው አድዋ ብቻ ተብሎ የቀረው፤ምንም እንኳ ውጊያው የተጠናቀቀበት አውራጃ ቢሆንም፤ይበልጥ በዘመናችን ጥቁሩ ወርቃማ የኢትዮጵያ ድል እየተባለ መጠራት ይገባዋል ።

Address

Reigate
RH68SA

Opening Hours

Monday 11am - 12pm
Tuesday 11am - 11pm
Wednesday 11am - 11pm
Thursday 11am - 11pm
Friday 11am - 2pm
Saturday 11am - 2pm
Sunday 11am - 11pm

Telephone

01293404620

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Injera le-tenaye posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share